BBC News, አማርኛ - ዜና

ዜና

ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ

አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ

በአጭሩ ይመልከቱ ይዝለሉ ቀጥሉ

በአጭሩ ይመልከቱ

  • ገዱ እንዳርጋቸው
  • ምሥል
  • ምሥል
  • ምሥል
  • ምሥል
  • ምሥል
  • ፎቶ
  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
  • ምሥል
  • የአቅራቢ እና የወታደር ምሥል
  • የመሪዎች ምሥል
  • ተማሪዎች

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ

የሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

    ኤርትራ "በሌሎች ኃይሎች ተማምና በጥፋት መንገድ የምትቀጥል ከሆነ ከባድ ውጤት እንደሚኖረው" ጠ/ሚ ዐቢይ አስጠነቀቁ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ሰላም እንደምትፈልግ እና የልማት አጋር መሆን እንደምትሻ ጠቅሰው፤ ኤርትራ "በሌሎች ኃይሎች ተማምና በጥፋት መንገድ የምትቀጥል ከሆነ ግን ከባድ ውጤት እንደሚኖረው" ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰኞ ጥቅምት 9/2013 ዓ. ም. በትግርኛ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር አጋርነት እንደምትፈልግ ተናግረው የማስጠንቀቂያ መልዕክትም ያስተላለፉት።

  • (ከግራ ወደ ቀኝ) ዶ/ር ቴዎድሮስ አረጋይ፣ ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ፣ አሰፋ አብርሃ፣ ⁠ዶ/ር ሺሻይ አማረ እና ረዳኢ ኃለፎም

    የትግራይ ባለአደራ አስተዳደር አምስቱ ተሿሚዎች እነማን ናቸው?

    መስከረም አጋማሽ ላይ ዳግም ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ አብዛኛው የትግራይ ክልል አካባቢ በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት እና በአጋር ኃይሉ ቁጥጥር ስር ገብቷል። ክልሉን በማረጋጋት እና መልሶ በመገንባት በምርጫ የሚመጣ አስተደዳር ቦታውን አስኪረከብ ድረስ ለስድስት ወራት የሚቆይ የባለአደራ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተሹሟል። አምስት አባላት ያሉት ይህ ባለአደራ አስተዳደርን የሚመሩት እና የመቀለ ከተማ ከንቲባ እንዲሆኑ የተሰየሙት አምስቱ ሰዎች እነማን ናቸው?

  • ማርኮ ሩቢዮ

    ህወሓትን "ተገንጣይ" ያሉት ሩቢዮ በአዲስ አበባ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር ተናገሩ

    የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ላለፉት ሦስት ሳምንታት ከፌደራል መንግሥቱ እና ከአጋሮቹ ጋር እየተዋጋ የሚገኘውን ህወሓት "ተገንጣይ ቡድን" በማለት በአዲስ አበባ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ እንደነበር ተናገሩ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ያላቸውን ስጋትም ገልጸዋል።

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና አምስቱ የባለአደራ አስተዳደር ተሿሚዎች

    የፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ክልል ጦርነቱ መጠናቀቁን ገልጾ የባለአደራ አስተዳደር መመሥረቱን አስታወቀ

    በትግራይ ክልል ለስድስት ወራት የሚቆይ ባለ አደራ አስተዳደር ተቋቋመ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ይህ ባለአደራ አስተዳደር በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ነጻና ግልጽ ምርጫ በማከናወን ትግራይ የፌዴሬሽኑ አካል የምትሆንበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት ተሰጥቶታል። በአስተዳደሩ ውስጥ በዋና አስፈጻሚነት ከተካተቱት መካከል የትግራይ ሰላም ኃይልን የሚመሩት ⁠ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ ይገኙበታል።

  • የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ

    ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ባለፉት 5 ወራት አሜሪካ የወሰደቻቸው 5 እርምጃዎች

    ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት አማካኝነት እንዲገታ ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት መካከል የአፍሪካ ኅብረት እና አሜሪካ ይጠቀሳሉ። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ዋነኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ምዕራባውያን አገራት አንዷ ናት። የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከሳምንታት በፊት ዳግም ሲቀሰቀስ ቀድመው መግለጫ ካወጡ አገራትም አንዷ ናት። አሜሪካ ከጦርነት መነሳት በፊት እና በኋላ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች እንደሚከተለው ቃኝተናል።

  • ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ

    ሶማሊላንድ በግብፅ የተመሠረተውን ጥምረት በመቃወም ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ገለጸች

    ሶማሊላንድ የኢትዮጵያን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት እና ጥምረትን እንደምትቃወም ገለጸች። ነጻ አገርነቷን ያወጀችው ሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ ከጎረቤታቸው ኢትዮጵያ ጋር ባላቸው ትብብር ከፍተኛ መተማመን እንዳላቸው ገልጸው "የኢትዮጵያን መረጋጋት እና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል የትኛውንም ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን" ብለዋል።

  • ሌ/ጄነራል ታደሰ፣ ኮሎኔል ተወልደ፣ ኮሎኔል ዓለምሰገድ እና አቶ ኢሳያስ

    'በሕይወት እንተርፋለን አላልንም' ፡ በህወሓት ቁጥጥር ስር የቆዩት የቀድሞ ባለሥልጣናት ምን ገጠማቸው?

    የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ፣ አራት የቀድሞ ባለሥልጣናት ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ከነበሩበት እስር አምልጠው በኢትዮጵያ ሠራዊት እጅ ከገቡ በኋላ ወደ መቀለ መመለሳቸውን ተናግረዋል። ባለሥልጣናቱ ዳግም የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በቀድሞ ጓዶቻቸው ከየቤታቸው ታግተው ከተወሰዱ በኋላ ያሳለፉትን እና እንዴት ሊያመልጡ እንደቻሉ ከመካከላቸው አንዱ ለቢቢሲ አጋርተዋል።

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩቢዮ ምን ተነጋገሩ?

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በስልክ ተወያይተዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ንግግራቸው ከኤርትራ ጋር "እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት" የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የውይይቱን ይዘት በዝርዝር ባይገልጹም "እጅግ ፍሬያማ" መሆኑን አስታውቀዋል።

  • ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ፣ ፕሬዝዳንት ሐሰን፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ

    ሶማሊያ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት ገለልተኛ መሆኗን ገለፀች

    የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ሐሰን ሞሐመድ አሊ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈጠረው ውጥረት አገራቸው "ገለልተኛ" መሆኗን ተናገሩ። ምክትል ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ከቢቢሲ ሶማልኛ ጋር እሁድ ጥቅምት 1/2019 ዓ.ም. በነበራቸው ቃለ ምልልስ ወቅት ነው።"የሶማሊያ መንግሥት አቋም ሰላማዊ እና ገለልተኛ ነው" ያሉት ሚኒስትሩ ከአገራቱ ጋር ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ትስስር እንዳለ ተናግረዋል።

  • የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናት በትናንትናው ዕለት በመቀለ እና አዲግራት ነዋሪዎችን አግኝተው ማነጋገራቸውን በመግለጽ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ መልዕክታቸውን አስፍረዋል

    ወደ ትግራይ የተጓዙት የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምን አሉ?

    በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በትናንትናው ዕለት ሲጀመር የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ መቀለ እና አዲግራት በማምራት ነዋሪዎችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ከ18 ወራት በኋላ ወደ ክልሉ ዋና መዲና መመለሳቸውን ሲናገሩ፣ ዶ/ር አብርሃም በላይ ደግሞ "ሰላም የተጠማው ሕዝባችንን ጎበኘነው” ብለዋል። የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው በመቀለ እና አዲግራት በነበራቸው ቆይታ "ጥልቅ የሰላም ጥማት" ማየታቸውን ገልጸዋል።

የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?

የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!

የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች

ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ

አነጋጋሪ ጉዳይ

ከየፈርጁ

አጃኢብ!

የተመለሱ ጥያቄዎች

ሌላ ዕይታ

በስፋት የተነበቡ